Tigrai Police
Tigrai Police
Tigrai Police

የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ፀብ -ጫሪነትን በመሸሽ ወደ አማራ ክልል በመግባት ላይ መሆናቸው ተገለጸ

የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ፀብ ጫሪነት በመሸሽ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ አማራ ክልል የሚገቡ የክልሉ የልዩ ኃይል አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።

የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይሎች የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ፀባ ጫሪነት በመሸሽ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ አማራ ክልል እየሸሹ ነው። ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

ከሰሞኑ ብቻ በሰሜን ጎንደር ከሰላሳ የሚበልጡ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የአጥፊነት መልዕክትን በመክዳት ወደ አማራ ክልል ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው መግባታቸውን ያስታወቁት ኃላፊው፤ ከነዚህ መካከል አንዳንዶች የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ያለባቸው የክልሉ ነዋሪዎች ልጆች መሆናቸውን አመልክተዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ የትግራይ ክልል ተወላጆች መሆናቸውን ገልጸዋል።ይህም ክልሉልዩ ኃይሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ መፈረካከስ እንዳለ አመላካች ነው ብለዋል።

ከትግራይ ክልል መንግሥት ሸሽተው የሚመጡት ዜጎቻችን በመሆናቸው ክልላችን በሚታወቅበት እንግዳን በአክብሮት የመቀበል ባህላችን ተቀብሎ እንክብካቤ እያደረገላቸው ነው ብለዋል።

ህወሃት በአሁኑ ወቅት በርካታ ወጣቶችን በወታደርነት በመመልመል ለጦርነት እያዘጋጀች መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፣ የትግራይ ሕዝብ የክልሉ መንግሥት እያደረገ ያለው ትክክል አይደለም ብሎ እንደሚያምን በፈቃዳቸው ወደ አማራ ክልል ከገቡ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት መረዳት መቻሉን አስታውቀዋል።

በግዳጅ የሚታጠቁ ወጣቶች ከእነ ትጥቃቸው በተደጋጋሚ ወደ አማራ ክልል እየገቡ ናቸው።በአማራ ክልል በኩል በእንደዚህ ዓይነት መልኩ ሰው እንዲመጣ አንፈልግም።ምክንያቱም ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት ብለን እናምናለን ሲሉ ኃላፊው አመላክተዋል።

ከትግራይ ክልል ጋር በምንዋሰንበት አካባቢ ለእረጅም ጊዜ የቆየ የአማራ ክልል ጥያቄ የሆነ የማንነት እና የወሰን ጥያቄ መኖሩን የጠቆሙት ኃላፊው፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የህወሃት የአድዋ ቡድን የጦርነት ዝግጅት ለሀገር እድገት እና አንድነት ተገቢ አይደለም ብለዋል። በድንበር አካባቢ ወደ ጦርነት ለመግባት የማኮብኮብ ዓይነት እንቅስቃሴዎች መኖራቸውንም አመልክተዋል።

«የአማራ ክልል ወደ ጦርነት አይገባም። የአማራ እና የትግራይ ሕዝቦች ሁለት ወንድማማች ሕዝቦች ናቸው።በግልፅ እንደሚታወቀው አብረው ተጋብተው እና ተዋልደው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው።ምንም ዓይነት ጉንተላ እና ፀብ-ጫሪነት በትግራይ ክልል መንግሥት በኩል ቢኖርም መቼም ቢሆን ሁለቱ ሕዝቦች ወደ ጦርነት ይገባሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው» ብለዋል ።

ከአማራ ክልል በኩል እስከዛሬ ድረስ ምንም ዓይነት ትንኮሳ የለም ወደፊትም አይኖርም የሚሉት ኃላፊው፤ በእኛ በኩል እየጠየቅነው ያለው የሕዝብ ጥያቄ የሆነውን የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ነው። ይህ ደግሞ ሕጋዊ ጥያቄ ስለሆነ ጉዳዩ የሚመለከተው የፌዴራሉ መንግሥት ሕጋዊ አሠራር ተከትሎ የራሱን እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል እንጠብቃለን ሲሉም ተናግረዋል።(ኢፕድ)

By admin

Ethiopians Today is Ethiopian #1 News Website. It is multilingual website that will share news update across the country and East of Africa. We have multiple authors over the World and actively working to release news updates about all Ethiopian nations. We believe in equality of all Ethiopian Nation, Nationalities, and People.

Leave a Reply

Advertisements