በትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎት ሲቋረጥ የሚያሳየው የሲሲቲቪ ካሜራ ምስል ተለቀቀ


በትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎት ሲቋረጥ የሚያሳየውን የሲሲቲቪ ካሜራ ምስል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ይፋ አድርጎታል።
በትግራይ ክልል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የኮሙዩኒኬሽን መቋረጥ ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል።


ብቸኛው የቴሌኮም አቅራቢ የሆነው ኢትዮ-ቴሌኮም ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች ሆነ ብለው ኔትወርክ እንዲቋረጥ ሲያደርጉ የሚያሳይ የሲሲቲቪ (CCTV) ካሜራ ቅጂ ከሰሜን ሪጅን ጽ/ቤት ያገኘ መሆኑንም ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር።


ጋቢ የለበሱ የኢትዮ-ቴሌኮም የሰሜን ሪጅን የጥበቃ ሠራተኞች በእነዚህ ባልታወቁ ሰዎች ተገፍትረው ከግቢ ሲወጡ በካሜራው ላይ ይታያል።
የጥበቃ ሠራተኞቹ ከግቢው ወጥተው ሌሎች ሰዎች ግቢውን ሲቆጣጠሩ እና ሌሎች ሰዎች ደግሞ ወደ ግቢው ሲገቡ ይታያል።
እነዚህ ሰዎች በቀጥታ የሳይቱ ዋና ሲስተም ወዳለበት ክፍል በማምራት ያቋርጡታል። ዋና ጽ/ቤት ያሉ የኢትዮ-ቴሌኮም ሠራተኞች እየሆነ ስላለው ነገር የሚያውቁት ነገር አልነበረም።


ሠራተኞቹ ያሰቡት የባትሪ ችግር የተፈጠረ ወይም ጄኔሬተሩ በትክክል መሥራት ያቆመ መስሏቸው ነበር።
ከሲሲቲቪ ካሜራ የተገኘው ምስል እንደሚያሳየው ግን ሲስተሙ የተቋረጠው በቀጥታ ወደ ቦታው በማምራት ሆነ ብለው በዘጉት ሰዎች ነው።
እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሁሉም ሲስተም ሲዘጋ የሲሲቲቪ ያለበት ክፍል ኃይል አልተቋረጠም ነበር። በሲሲቲቪ ካሜራ የተያዘው ምስልም ሳይሰረዝ ተገኝቷል።


ካሜራው እስከ ጥቅምት 25 ከቀኑ 10 ሰዓት ከ20 ድረስ ሲቀርፅ የነበረ ሲሆን የመጨረሻ ምስሉም አንድ ግለሰብ ወደ ክፍሉ ገብቶ ካሜራውን እስኪያጠፋው ድረስ የነበረውን ሂደት ያሳያል።

Image may contain: text that says '11 04 2020 Ued 00:50:47 People at the head office didn' know what went wrong'
Image may contain: one or more people and outdoorImage may contain: one or more people, text that says '2020-11-04 Wed 01:01:50 was not and we found this record without being erased. YROD-D001'Image may contain: one or more people, text that says '11/01/202 Ued 00:56:14 By chance while everything was shut down the power to the CCTV room oom08'Image may contain: one or more people, text that says 'where main for the core is located. GFYROD-'Image may contain: one or more people, text that says 'As you can see, they were been pushed out of the compound'
Become a Sponsor

By admin

Ethiopians Today is Ethiopian #1 News Website. It is multilingual website that will share news update across the country and East of Africa. We have multiple authors over the World and actively working to release news updates about all Ethiopian nations. We believe in equality of all Ethiopian Nation, Nationalities, and People.

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x
Advertisements