ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የቀረበባትን ክስ አሸነፈች

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እስራኤል ኬሚካል ሊሚትድ “ICL” በተባለ የፖታሽ ማዕድን አውጪ ኩባንያ የተመሰረትባትን ክስ ማሸነፏን የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአፋር ክልል በዳሎል አካባቢ በፖታሽ ማዕድን ልማት ስራ ላይ ተሠማርቶ የነበረው አይ ሲ ኤል የተሠኘው የእስራኤል ኩባንያ በአለምአቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ መስርቶት በነበረው የ300 ሚሊዮን ብር የካሳ ጥያቄ ክርክር ተረትቷል።

አይ ሲ ኤል የኢትዮጵያ መንግስት አላግባብ የፖታሽ ማዕድን ልማት ፕሮጀክት አቋርጦብኛል በማለት የ300 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈለው የመሠረተው ክስ በትናንትናው ዕለት ውድቅ እንደተደረገበት የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል።

ፍርዱን የሰጠው በሄግ ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት ሲሆን ይግባኝ የማይባልበት ፍርድ መሆኑ ተነግሯል።
በክርክሩ ሂደት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳታፊ ለነበሩ ሁሉ የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስቴር ምስጋናውን አቅርቧል።

Source: EBC

Become a Sponsor

By Chala Dandessa

Chala Dandessa is Founder of Ethiopians Today Website. Ethiopians Today is Ethiopian #1 multilingual news website in Ethiopia. Ethiopians Today is Ethiopian #1 News Website. It is multilingual website that will share news update across the country and East of Africa. We have multiple authors over the World and actively working to release news updates about all Ethiopian nations. We believe in equality of all Ethiopian Nation, Nationalities, and People.

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x
Advertisements