“የህወሓትን ቡድን”ይደግፋሉ ያላቸውን 323 ግለሰቦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ

ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎቹ በብሔራቸው ምክንያት ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት የሚለው ወሬ የተሳሳተ ነውም ብሏል

ኢሰመኮ በሀገሪቱ በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚደርስ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስር እና እንግልት እንዳለ የሚያሳዩ መረጃዎች እየደረሱት መሆኑን ገልጾ ነበር
“የህወሓትን ቡድን” በመደገፍ በተለያዩ የተግባር እንቅስቃሴዎች ተሰማርተዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 323 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ደበላ “ግለሰቦቹ ከተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች መካከል አሸባሪው የህወሀት ድርጅትን መደገፍ፣ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት፣ ሕገመንግስቱን ማንቋሸሽ፣ ሰንደቅ ዓላማን ማዋረድ፣ ኃሺሽ ማጨስ እና ቁማር መጫወት ይገኙበታል” ማለታቸውን ኢቲቪ ዘግቧል፡፡
በወንጀሎቹ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መኖሪያ ቤት በፍርድ ቤት ፍቃድ በተደረገው ፍተሻ የህወሀት ልዩ ኃይል አልባሳት፣ ሽጉጦች፣ ክላሾች እና ጥይቶችን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቤታቸው መገኘቱንም ኮሚሽነሩ ገልጿል፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የንግድ ድርጅቶችም ታሽገው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑም አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ አንዳንድ አካላት እንደሚገልፁት በብሔራቸው ምክንያት ሳይሆን በቁጥጥር ስር የዋሉት በትክክልም ወንጀል ፈፅመው በመገኘታቸው ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ።

ከተማዋን የጥፋት ቀጠና ለማድረግ “አሸባሪ ቡድኑን” በመደገፍ የሀገርን ሰላም ለማናጋት የሚያስቡ ካሉ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት ኮሚሽነሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የህግ የማስከበሩ ስራ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ከትናንት በስትያ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚደርስ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስር፣ የንግድ ቤት መዘጋት እና የእንግልት መረጃዎችን እየሰረሱኝ እየደረሱት እንደሆነ ከቀናት በፊት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
የሚድያ ሰራተኞችን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች እየተወሰዱ መሆናቸውንም ኮሚሽኑ ጥቆማዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡

ከሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተባብሶ የታየው ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ክስተትና እስር ሁኔታ ተገቢውን ትኩረትና መፍትሔ ካለማግኘቱ በተጨማሪ፤ በስፋት የሚደመጡ የጥላቻና ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ሁኔታውን ሊያባብሱና ብሎም በማሕበረሰብ መካከል ያለውን ትስስር ሊያላሉ እንደሚችሉም ኢሰመኮ ጠቅሷል።

በመሆኑም በየትኛውም አካባቢ ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ ነዋሪዎች በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁና የፌዴራል መንግስትም ሆነ የክልል መስተዳድሮች በነዚህ ነዋሪዎች ላይ እንግልት ያደረሱና ሌሎች ሕገወጥ ድርጊቶች የፈጸሙ የሕግ አስከባሪ አካላትን በሕግ ፊት እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
የኢሰመኮ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በዚህ ፈታኝና የውጥረት ወቅት መንግስት ለሲቪል ሰዎችና ተጋላጭ ለሆነው ማኅበረሰብ ክፍል ከፍተኛ ጥበቃ የማድረግ ተጨማሪ ኃላፊነት የሚጣልበት መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

Become a Sponsor

By Chala Dandessa

Chala Dandessa is Founder of Ethiopians Today Website. Ethiopians Today is Ethiopian #1 multilingual news website in Ethiopia. Ethiopians Today is Ethiopian #1 News Website. It is multilingual website that will share news update across the country and East of Africa. We have multiple authors over the World and actively working to release news updates about all Ethiopian nations. We believe in equality of all Ethiopian Nation, Nationalities, and People.

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x
Advertisements