“መቐለን የመልቀቅ ውሳኔ ከወታደራዊ ትርፍና ኪሳራ አኳያ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው”- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

“መቐለን የመልቀቅ ውሳኔ ከወታደራዊ ትርፍና ኪሳራ አኳያ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው”- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

መቐለን የመልቀቅ ውሳኔ ከወታደራዊ ትርፍና ኪሳራ አኳያ ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ ገለጹ፡፡
ጉዳዩን በማስመልከት የመከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በጋራ ሰጥተዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስቴር የሰራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የጁንታው ኃይል የትግራይን ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር እንዲጋጭ እያደረገው ነው ብለዋል፡፡


ቡድኑ በሽምቅ ውግያ መከላከያ ሰራዊቱን ማሻነፍ ስለማይችል ህዝቡን ከፊት አድርጎ መከላከያ ሰራዊት ጋር ማጋጨትን እንደ ዘዴ መጠቀሙን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደባሌ ገልጸዋል፡፡
መቐለ ከተማ መጀመሪያ መከላከያ ሲገባና አሁን ከስበት ማዕከልነት አንፃር የተለያየ መሆኑን ሌ/ጄ ባጫ አስረድተዋል፡፡
መንግስት በትግራይ ክልል ያደረገው የተናጥል የተኩስ አቁም እርምጃ በመንግስት የተወሰደ ፖለቲካዊ ውሳኔ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።


የፖለቲካ ውሳኔው ተቀይሮ መቐለ መግባት አስፋላጊ ሆኖ ከተገኘ አሁንም መግስት መግባት እንደሚችል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የገለጹት፡፡
የትግራይ ክልል አርሶ አደሮች የመኸሩ ጊዜ ሳያልፍ ወደ እርሻ እንዲገቡ ያለመ ውሳኔ መንግስት መሰጠቱንም ነው አምባሳደሩ የተናገሩት።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ ዓለም አቀፍ ጫና ለመቀነስም ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

 44 total views,  3 views today

About Chala Dandessa

Name: Chala Dandessa. I was born in West Shewa Zone, Chobi District of Oromia Region, Ethiopia in 1989. Founder of Ethiopians Today Website Currently I am Lecturer at Jimma Teachers College. Peace and Unity for our country! https://ethiopianstoday.com

View all posts by Chala Dandessa →

Leave a Reply