Tue. Apr 23rd, 2024

Loading

”ኦሮሙማ ይውደም!” የዳግማዊ ሁቱዎች መፈክር-By Merid Tullu

~ቱትሲዎችን ባገኛችሁበት ሁሉ ግደሉአቸው~

ኦሮሙማ ማለት ኦሮሞ መሆን ነው። ኦሮሞ መሆን ደግሞ ሰው መሆን፣ አፋን ኦሮሞ መናገር፣ የኦሮሞን ባህል እና እሴት ማወቅ እና ማክበር፣ ፈጣሪን ማክበር ነው።

ኦሮሞ አድርጎ የሚፈጥር እግዚአብሔር ነው። ማንኛውንም ሰው የሚፈጥረው ዋቃ/እግዚአብሔር ”ኡማ ኡማማ ሁንዳ ቡልቻ ሩዳ” ሁሉን ፈጥሮ የሚያስተዳድር ብሎ ለዝንተ አለም በኦሮሞ ዘንድ እየታመነ ዛሬ ደርሷል።

የዛሬ 17 ዓመት ሁቱዎች በሪዋንዳ የጅምላ ጭፍጨፋ ሲፈፅሙ መጀመሪያ ላይ ያደረጉት ቱትሲዎች ሰው አይደሉም፣ ይገደሉ በማለት ጀመሩ። በቲቪ፣ በሬዲዮ በባነር አስተዋወቁ። ከዛ ወደ ጭፍጨፋ ገብቶ ወደ 100000 ቱትሲዎችን ገደሉ። ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ፣ የሰው ሬሳ እንደ ተራራ ተከመረ፣ ሀገሪቷ ዘቀጠች። በኋላ ላይ አስከፊው ጦርነት አለቀ። ዛሬም ኦሮሞ ላይ ሊያደርጉት ያሰቡት ሌላ አይደለም። ይህንኑ ነው።

ዛሬ ኦሮሙማ ይውደም ያሉት ሰዎች ከመሬት ተነስቶ አይደለም። አስቦበት አስልቶ ነው እንጂ። በጨለማ ያሰቡትን ወደ ገሀድ አወጡ። በጣም የቆየ ፕሮጀክት በመሆኑ ማንም ኦሮሞው መነሻውን ማወቅ አለበት። ትንሽ እንዘርዝር
1. በሚዲያ ኦሮሙማን ሲሳደቡ ሲያንቋሽሹ ነበሪ። እነ ኤርሚያስ ለገሰ፣ ታምራት ነገራ፣ ሀብታሙ አያለው፣ ኢትዮ 360፣ ኢሳት፣ EBC, FANA, WALTA, ወዘተ ኦሮሙማ ላይ ጦርነት አውጆ ለተከታታይ ሶስት አመት ዘምቶብናል። የመንግስት ሚዲያ እንኳን ሀጫሉ በተሰዋበት ሰሞን የነበሩበትን ሁነታ አስቡ።

  1. ለ800 ዓመታት ኦሮሙማን ለማጥፋት ተሞክሯል። ከ7ኛ ክ/ዘን የተጀመረው። በ16 ክ/ዘ ኦሮሞ ተደራጅቶ መክቶ መሬቱን ቢያስመልስም ሞኖክሴ እንኳን ሳይቀር ለታላቁ ኦሮሞ ህዝብ ስም እየሰጡ 19ኛ ክ/ዘ ደርሰናል። በ19ኛ ክ/ዘ ኦሮሞ፣ ኦሮሚያን እና ኦሮሙማን ለማጥፋት በብዙ ተሰርቷል። ብዙ ኦሮሞዎችን ገድሏል፣ እጅ እና እግር ቆርጧል። የኦሮሞን መሬት በራሳቸው ስም ጠርቷል፣ አፋን ኦሮሞን በህግ ከልክሏል።

  2. ኦሮሞ ሀብት እንዳያፈራ፣ እንዳይማር ተሰርቷል። ዛሬ ሰልፍ ወጥቶ ኦሮሙማ ይውደም ያሉት ሰዎች የሚያሞካሹት ነገስታቶቻቸው ”ፈፅሞ ኦሮሞ መማር የለበትም፣ ኦሮሞ ከተማ መግባት የለበትም፣ ኦሮሞ ቤተእምነት ውስጥ መሪ እንዳይሆን፣ ኦሮሞ የእነሱ አሽከር እንድሆን ብቻ ሰሩበት”

  3. ኦሮሞ ከፖለቲካ እንድወጣ dehumanize እያደረጉ ከፖለቲካ አለም እንድገለል ሰርቷል።ዛሬም አስሯል፣ አሳስሯል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ኦሮሞን ለማጥፋት የተሰራ ያህል ሩቡ እንኳን ለሀገር ለውጥ፣ ለራሳቸው ህዝብ መለወጥ ብሰሩ የት በደረሱ ነበር።

ኦሮሙማ
ኦሮሙማ ውስጥ ኦሮ-ኡማ በፈጣሪ የተፈጠረ፣ የተከበረ ሰው የሚል ፍቺ አለ። ኦሮሙማ የሚወድመው ፈጣሪ ስራውን ያቆመ ቀን ብቻ ነው። ኦሮሙማ ውስጥ የእግዚአብሔር ሀይል አለ። ሰው ምንም ያህል ብለፋ ኦሮሙማን ሊያጠፋ አይችልም።

ኦሮሙማ የአለም civilization በኩር፣ የአስትሮሎጂ ሳይንስ ባለቤት፣ የስነ ህሳብ እና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ባለቤቶች ናቸው። ትናንት ከሚሲራ እስከ ግሪክ፣ ከሜሶፖታሚያ እስከ ኢራን፣ ከሜሮኤ እስከ ፑንት እስከ ሴኔጋል (Seene gali) ሲቪላይዜሺንን አስተምሯል። የግብጥ Hieroglyphics በአፋን ኦሮሞ እንደተጻፈ፣ የግብጥ እና ሜሮዔ ጡቦች በአፋን ኦሮሞ እና ገዳ ምስሎች እንደተጻፉ እና ተሞሉ ማየት ይቻላል።

ኦሮሙማ
ልጅ ሆነን በEebba Oromoo, በኦዱ ዱሪ፣ በሂቦ፣ በሳፉ፣ ያነጸን ስርዓት ነው። ለሁሉም ሰው በየእድሜው ተጠያቂነት መስጠት፣ ለተፈጥሮ ሁሉ ርሩህ መሆን፣ ሰውን መውደድ እና ማክበር፣ ከራስ በላይ ለሌላ መሆን ነው።
ኦሮሙማ ውሃ ስጠየቅ ወተት መስጠት ነው። ኦሮሙማ ለባህር እንስሳት፣ ለዱር እንሰሳት እና ለቤት እንሰሳት ማሰብ ማንከባከብ ነው።
ኦሮሙማ
ኦሮሙማ ሌሎችን መውደድ እና የሆነውን ኦሮሙማን እንኳን መስጠት ነው። ኦሮሙማ ፈጣሪን መውደድ እና ማክበር ነው። ኦሮሙማ እውነት እና ሰላም ነው። ኦሮሙማ እየተበደለም ብሆን መቻል፣ ይቅር ማለት ነው። ኦሮሙማ ታላቆችን ማክበር፣ ለተቸገሩ መድረስ ነው።

ኦሮሙማ ለኦሮሚያ መሞት ነው። ኦሮሞ ኦሮሙማን ከፈጣሪ ያገኘ ማንነቱ እንደሆነ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያውቀዋል። ለኦሮሙማ መሞት ካለበት ደስ ብሎት ያደርጋል።
ኦሮሙማ
ኦሮሙማ የወንዝ ዳር አበባ ነው። ሁለ ያለመልም ይሆናል እንጂ አይወድም። ኦሮሙማ 73 ሚሊዮን ሰው ነው። ከኢትዮጵያ እስከ ኬኒያ፣ ከታንዛኒያ እስከ ዩጋንዳ ያለ ማንነት ነው። ዛሬ ኦሮሞ ባለበት ሁሉ ኦሮሙማ አለ። ያኔ ከገባር እና እምፔሪያልስት ያልጠፋ ማንነት ዛሬ ልጆቹ በበዙበት ወቅት ኦሮሙማ ይጠፋል ማለት ጸሐይን እንዳትወጣ የመከልከል ያህል ማፈዝ ነው።

ገና ስንወለድ ኦሮሞ ነበርን፣ በኦሮሙማ አደግን። በወጣትነታችን በኦሮሙማችን ደምቀን አለን። ኦሮሙማ እቃ አይደለም። ኦሮሙማ ልብስ አይደለም። ኦሮሙማ ህንፃ አይደለም። ኦሮሙማ ሰብዓውነት ነው። ሰው መሆን ኦሮሞ መሆን ነው።

ኦሮሙማን ማንኛውም ምድራዊ ሀይል ልደመስስ አይችልም። በፈረንሳይ መሳሪያ፣ በጣሊያን ደሞፍተር፣ በእንግሊዝ ቦምብ፣ በራሺያ ክላሽንኮቭ፣ በአሜሪካ ሄሊኮፕተር ሞክረዋል። የባሌ ገበሬዎች ላይ፣ የወለጋ ህዝብ ላይ፣ የሸዋ ተለማ ላይ፣ የባሌ እና አርሲ ሲኮ ማንዶ ላይ፣ ኢቱ እና ሁምበና ላይ፣ የወሎ ኦሮሞ ላይ ”መደምሰስን ሞክሮ ተደምስሷል”።

ኦሮሙማ ገና ይለመልማል
ኦሮሙማ ገና ያብባል
ኦሮሙማ ገና ከፍ ይላል
ኦሮሙማ ገና ለአለም በብዙ ተምሳሌት ይሆናል።

ይቺ ምስል የዛሬ ሰባት አመት የተወሰደች ናት። ያኔ የነበረው system የኦሮሞ ባህል ልብስ መልበስ እስከ ማሳሰር ያደርስ ነበር። ያንን ስርዓት ቀብረነዋል። እነ ደምሳሽ እና ደመላሽንም በኦሮሙማችን ከመጡብን ለመቅበር ዝግጁ ነን።

ሙአዘጥበባት ነኝ
ከሰላም ዛፍ ኦዳ ስር
ፊራ ኦሮሞ ማራ

Follow us on:

YOUTUBE  FACEBOOK TELEGRAM GOOGLE NEWS TWITTER  INSTAGRAM PINTEREST

Subscribe and Follow us via Email

If you have any comment regarding this article contact us at contact@ethiopianstoday.com

By Chala Dandessa

I am Lecturer, Researcher and Freelancer. I am the founder and Editor at ETHIOPIANS TODAY website. If you have any comment use caalaadd2@gmail.com as email contact. Additionally you can contact us through the contact page of www.ethiopianstoday.com.

Leave a Reply