Fri. Oct 4th, 2024
Сollaborator

Loading

የጠቅላይ- አግላዩ ጣዕረ ሞት!

የጠቅላይ- አግላዩ ፀረ-ስልጣኔ ስብስብ ቁንጮዉ አብን ዛሬ ኦሮሙማን (ኦሮሞነትን) ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እንደሚታገል አቋሙን ገልጿል። ድንገት ድብቅ ማኒፌስቶዉን ነግሮናል! ከከከ..የጠቅላይ-አግላዩ ጣዕረ-ሞት ከንቱ ምኞት በጣም ይገርማል! በሰዉ ጠል ፀረ-ስልጣኔዉ እሳቤ ለ150 ዓመታት የተሰራበትን እጅግ አደገኛ ሴራ አሸንፎ ህብረ-ብሔራዊነት፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነት በኢትዮጵያ እንዲሰፍኑ መንገድ የከፈተዉ ኦሮሙማ (ኦሮሞ) አሁን ላይ እንዴት ተደርጎ ይጠፋል? በእርግጥ ማሰብያዉ የታወረ ድንዙዝ ፓርቲ መች ሁኔታን ማንበብ ይችላል? ከ17ኛዉ ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ ጋር ቆርቦ ያላዝናል!

የጠቅላይ-አግላዩ መንፈስ ብዙህነትን አጥብቆ ይጠላል። የኢትዮጵያ ብሔር-ብሔረሰቦችን በመጥፋት አንድ ልሙጥ ማንነት ለመፍጠር ፖሊሲ አዉጥቶ ለዘመናት ሠርቷል። እያንዳንዱ ብሔር ማንነቱን እንዲክድ የስድብ ስም አዉጥቶለት ሲያሸማቅቅ ኖሯል።

ወላይታን ወላሞ፣ ጋሞን ዶርዜ፣ ጌድዎን ደራሳ፣ ጉሙዝንና በርታን ሻንቅላ፣ ኦሮሞን ጋላ፣ አኟንና ኑዌርን ባርያ፣ ሶማሌንና አፋርን ሽርጣም፣ ትግራዋይን አጋሜ እያለ ሁሉንም ንቆ የጠቅላይ-አግላዩን የሰዉነት ዉሃ ልክነት ሰብኳል! ይህ አተያይ ግን ከዘመናት በፊት በህዝቦች ጠንካራ ትግል ታሪክ ሆኗል! ዛሬ ላይ ድንዝዙ አብን ከሞተ ዓመታት ያለፉበትን መንፈስ ይዞ ብቅ ሲል ያስቃል! ዘና ብሎ "ኦሮሞነት ይዉደም" ሲል ጨቅላነቱ ያሳብቃል! ይህ ማለት ደግሞ "ወለይታነት፣ ሶማሌነት፣ ጉራጌነት፣ ሲዳማነት፣ አኟነት፣ ኑዌርነት፣ አፋርነት፣ አገዎነት፣ ጉሙዝነት፣ በርታነት፣ ትግራዋይነት፣ ሀረሪነት፣ ሀድያነት፣ ካምባታነት ወዘተ ይዉደምና የጠቅላይ-አግላዩ ልሙጥ ማንነት ብቻ ይለምልም" ማለት እንደሆነ ልብ ይሏል! በርግጥ ይህ አሳፋሪና ሞኛ ሞኝ አመለካከት ጨዋዉን የአማራ ህዝብ እንደማይወክል በደንብ መታወቅ ይኖርበታል። ይልቁንም በአማራ ስም የሚሰበክ ፀረ-አማራ ፖለቲካ መሆኑን አፅንኦት መስጠት ያስፈልጋል!

ሲጠቃለል አብን በኢትዮጵያ ፖለቲካ መኖሩ ደስ ይላል! ያለምንም ድካም የ17ኛዉን፣ የ18ኛዉንና የ19ኛዉን ክፍለ ዘመን ፖለቲካ ያስታዉሰናል!

For further information follow us on:
Facebook Twitter Telegram Instagram Google News

If you have any complain contact us at contact@ethiopianstoday.com 

By Chala Dandessa

I am Lecturer, Researcher and Freelancer. I am the founder and Editor at ETHIOPIANS TODAY website. If you have any comment use caalaadd2@gmail.com as email contact. Additionally you can contact us through the contact page of www.ethiopianstoday.com.

Leave a Reply

Сollaborator