Sat. Sep 23rd, 2023

በአሶሳ መንበረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ካቴዴራል ግቢ ውስጥ ከ35 ዓመታት በላይ ተቀብሮ የኖረ ከ624 በላይ የዙ 23 ተተኳሽ ጥይት ተገኘ

በአሶሳ ሀገረ ስብከት በመንበረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ካቴዴራል ቤተ-ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ35 ዓመት በላይ ተቀብሮ የኖረ ጥይት በልማት ስራ ቁፋሮ ላይ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

የአሶሳ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መልዓከ ጸሀይ ቆሞስ አባ ዘካርያስ ጸጋው የተገኘውን ጥይት አስመልክቶ እንደገለጹት አካባቢው ከዘመነ ደርግ በፊትም ሆነ በኋላ የጦር ሰፈር እንደነበርና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ማከማቻ ቦታ እንደነበር እና ከሚመለከተዉ የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ቦታዉ ለቤተ-ክርስቲያን አምልኮት እንደተሰጠና ቤተክርስቲያኗ ቦታዉን አስከብራ በመቆየቷ ከ35 አመት በላይ ተቀብሮ የቆየ ጥይት መሆኑን ገልጸዉ፣ ጥይቱ በዚህ መንገድ የተገኘ መሆኑን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል፡፡

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮ/ር ቡሽራ አልቀሪብ ስለጉዳዩ ሲያብራሩ ቦታዉ ለቤተክርስቲያን ልማት ከመዋሉ በፊት የደርግ 47ኛ ክፍለ ጦር የነበረበት ቦታ እንደነበር እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ማከማቻ ሰፈር እንደነበር ገልጸዉ ዛሬ የተገኘዉ የዙ 23 ተተኳሽ ጥይት በቁጥር 624 በላይ የሚሆንና ከ35 ዓመት በላይ በመሬት ዉስጥ ተቀብሮ የተገኘ የበሰበሰና አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኮማንደር ቡሽራ አክለዉም አካባቢዉ የቀድሞ ጦር ሰፈር መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ እዉነቱ እንዲረዳና በሌላ መንገድ እንዳይወሰድ ሲሉ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

የአሶሳ ከተማ አስተዳድር ኮሙዩኒኬሽን

By Chala Dandessa

I am Lecturer, Researcher and Freelancer. I am the founder and Editor at ETHIOPIANS TODAY website. If you have any comment use caalaadd2@gmail.com as email contact. Additionally you can contact us through the contact page of www.ethiopianstoday.com.

Leave a Reply