የአውሮፓ ህብረት ሴራ በኡጋንዳ
የአውሮፓ ህብረትም ሆነ ምዕራቢያውያን በሚል ስያሜ የሚመደቡ አካላት በተለየ ሁኔታ እኛ እናውቅላችኋለን በሚለው የበላይነት መገለጫ እብሪት ደጋግመው ይሳሳታሉ። በተለይ ይህንን ከልክ ያለፈ የንቀት ዝልፊያ የሚያበራክቱት ከሰሐራ በታች ባሉ አፍሪካዊ ሀገራት ላይ እንደሆነ ይታወቃል።
ይህን ሰሞን እንኳ ኡጋንዳ ምርጫ ከማካሄዷ በፊት ጀምሮ ለማበጣበጥ ከፍተኛ ጥረተ ሲያደርጉ ነበር ። ቦቢ ዋይን የሚባለውን ታዋቂ የኪነት ሰው ከዩዌሪ ሙሴቪኒ ባፋለመው የዩጋንዳ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አውሮፓ ህብረት ታዝቦ ነበር። በግልፅ በሚባል ደረጃ ቦቢ ዋይን የተባለው ተቃዋሚ ተሸንፏል ፤ ሆኖም የአውሮፓ ህብረት ፍላጎት አልተሳካም ስለዚህም ይህንን ተቃዋሚ በራሱ ፈቃድ ቃለ መሃላ እንዲያደርግ ከጀርባ ሆኖ በዩጋንዳ መቀመጫውን ያደረገው አውሮፓ ህብረት ሲገፋፈ ከረመ።
ከዩጋንዳ የምርጫ ኮሚሽን እውቅና ውጭ በአውሮፓ ህብረት አይዞህ ባይነት የልብ ልብ የተሰማው ወጣቱ ቦቢ ዋይንም በግሉ እኔ የዩጋንዳ ህጋዊ ፕሬዝዳንት ነኝ ብሎ ቃለመሃላ ፈፀመ። አሁን በውስጥ በኩል ሾልኮ በወጣው መረጃ መሰረት የአውሮፓ ህብረት በዩጋንዳ አምባሳደሩ በኩል የጻፈው ደብዳቤ ህብረቱ ዩዌሪ ሙሴቪኒን ህጋዊው እና የተመረጠው የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት አድርጎ እንዳልተቀበለ ገልጾ ፤ ለቦቢ ዋይን በጻፈው ደብዳቤ አንተ የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ነህ ብሎ አውጇል።
አውሮፓ ህብረት እንዲህ ምርጫን ተገን ያደረገ ሿሚ ሻሪ ሚናውን በዩጋንዳ የሚያቆም እንዳልሆነ ይታወቃል። በሀገራችንም ምርጫ ላይ ምን እንደፈለገ ግልፅ ባልሆነ መንገድ አንዴ የሀገርን ልዑዓላዊነት የሚጋፋ ምክንያት በማቅረብ በስድስተኛው የሀገራችን ምርጫ በታዛቢነት አልሳተፍም ሲል የከረመው የአውሮፓ ህብረት፤ በቅርብ ደግሞ አሁን ባለው መልኩ በአባል ሀገራት የምርጫ ታዛቢ መሆን እንፈልጋለን ማለት ጀምሯል፤ በመቀጠል ደግሞ ምርጫው አሁን መከናወን የለበትም መራዘም አለበት የሚል ቅስቀሳ በኢንተርናሽናል ኮሚዩኒቲው አስታኮ እያደረገ ያለውም ይኼው የቅኝ ገዥ እብሪት የወጠረው አውሮፓ ህብረት መሆኑ እጅግ አስገራሚ ጉዳይ ሆኗል።
ሀገራችን በራሷ ጥረት ሪፎርሟን ከአደናቃፊውቿ አፅድታ ፤ የአምናውን የኮሮና ጥቃትንም ለህዝብ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት አሳልፋ፣ የውስጥ ተቸካይ ሽብርተኞች እና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ከልማቷም ሆነ ከሪፎርሟ ሊጎትቷት የቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። ሁሉንም እናልፈዋለን ፣ ምርጫውንም እናከናውናለን ፣ ሀገራችንንም ልክ እንደ ሺዎች አመታት ታሪኳ በድል በነጻነት እናስቀጥላታለን።
ቅኝ አልተገዛንም ፣ ቅኝ የተገዙትንም ሙሉ አፍሪካውያን ነፃ አውጥተናል ፤ አሁንም ማንንም ቢሆን በውስጣችን ጉዳዮች ጣልቃ አናስገባም ። አውሮፓ ህብረትንም ጨምሮ። ዩጋንዳ ማለት ኢትዮጵያ አይደለችም ። ምርጫውን እንደፈለጉ ማገንፋት በነፃዋ ኢትዮጵያ አይፈቀድም ።
Follow us on:
YOUTUBE FACEBOOK TELEGRAM GOOGLE NEWS TWITTER INSTAGRAM PINTEREST
Subscribe and Follow us via Email
If you have any comment regarding this article contact us at contact@ethiopianstoday.com