የአብን መግለጫ ሕገ መንግሥት ይቃረናል‼
አንቀፅ 29 (6) የአመለካከትና ሐሳብን በነፃነት የመያዝ መብት ላይ፤ "…የጦርነት ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በሕግ የሚከለከሉ ይሆናሉ።" የሚል ድንጋጌ ሰፍሯል።
አብን በማንኛውም መልኩ ሐሳቡን የማራመድ መብት ቢኖረውም፤ እንደ ፖለቲካ ድርጅት የተመሰረተበትን፣ የተደራጀበትንና በዴሞክራሲያዊ አግባብ እንዲወዳደር ዕድል የሰጠውን ሕገ-መንግሥት አክብሮ መንቀሳቀስ ይኖርበታል።
የጦርነት ቅስቀሳም ማድረግ አይችልም። "ሲሞቅ በማንኪያ፣ ሲቀዘቅዝ በእጅ" እንደሚባለው፤ ሕገ መንግሥቱን ለምርጫ ወቅት ሲሆን እየተጠቀመበት፤ የችግር ጊዜ ሲሆን እንዳሻው መደፍጠጥ አይችልም። በተጨማሪም ነገሮችን በሰከነ መንፈስ ማመዛዘን ይኖርበታል። ፖርቲው ሕጋዊ አካል በመሆኑ፤ ተጠያቂነት እንዳለበትም መዘንጋት የለበትም።
Toleeraa Caalaa
109 total views, 1 views today