Mon. May 27th, 2024

ሀገር ወዳድነት እና ሀይማኖትን ይዞ እስከ ቀራኒዮ


አቡነ ጴጥሮስ (መገርሳ በdhaሳ)
አቡነ ጴጥሮስ የተወለዱት በሰላሌ በግራር ጃርሶ ቱሉ ሰላሌ አጠገብ ነው። ስማቸውም መገርሳ በdhaሳ ነበር። የተወለዱበት ሰፈር የታላላቆቹ ሀገር የከበሩ ሽማግሌዎች፣ የእነ ወረ እጉ አቡ ሀገር ነው።


በልጅነት እድሜያቸው የሀይማኖት ትምህርት ተምረዋል። የአብነት ትምህርት ስጨርሱ ስማቸው ከመገርሳ ወደ ”ሀይለማሪያም’ ተቀይሮ ነበር። ተፈጥሮዓቸው በጣም የዋህ እና ልበ ቅን ስሆኑ በ24 ዓመታቸው ስርዓተ ሙንክስና ተቀበሉ።
በጣም ጎበዝ አገልጋይ ስለ ነበሩ በወጣትነታቸው በወላይታ አንድን ገዳም ያስተዳድሩ ነበር። ኤጵስ ቆጶስ ሆኖ የባቱ ገዳማትን አገልግለዋል። ይህንን ያዩት በጊዜው የነበሩት ፓትርያርክ በ1921 ከሀገረ እስክንድርያ ጵጵስናን እንወሰዱ አደረጉ። አቡነ ጴጥሮስም ተባሉ። ከዛ በወሎ ክፍለ ሀገር አገለሉ።
በወሎ የሙስሊሙን ህብረት ሰብ እና ክርስቲያኖች መካከል ጥሩ ግንኙነት እንድኖር አደረጉ። ከህዝብ ጋር በጣም ተቀራርቦ ይሰሩ ነበር። በተለይ ከወረ ባቦ፣ ወረ እሉ እና ወራ ቃሉ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ቤተሰባዊ ነበር


በ1935 ጣሊያን ማይጨው ላይ የሀይለሲላሴን ጦር ሲያሸንፍ ንጉሱ ቤተሰቦቻቸውን እና ዘመዳቸውን ሰብስቦ ወደ ሀገረ እግልዝ ፈረጠጠ። በዝህ ግዜ ነው የበረሀው ሞኖክሴ መስቀሉን ተሸክሞ መፅሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ ፋሽስት ጠላትን ለመቃወም እና ለመፋለም ወሰኑ። ያ ሰው የሀገር ጳጳስ አቡነ መገርሳ ነበሩ።
ከህዝብ ጋር የነበራቸው ፍቅር ወደር አልነበረውም።


ጠላት ጣሊያን ዜጎቻቸውን እንደገደሉ ባዩ ግዜ ግራዚያኒን ለመውገዝ ከወሎ ወደ መሀል ሀገር መጡ። ፋሺስቶችም ህዝቡ እንድገዛልን አሳምኑልን ባላቸው ግዜ አቡነ ጴጥሮስ
”አንተ ፋሽስት እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ መሬቱም እንዳይገዛልህ ገዝቻለሁ” አሉት።
በዚህ መሀል ከጀግናው አብቹ በየነ ጋር ይገናኛሉ። አብቹ ሄዶ ጦሩን እንድያዘጋጅ ይመክሩት እና እራሳቸው ወደ ደብረ ልባኖስ ገዳም ሄዱ። ፀሎት አድርጉ ክፉ ጠላት ሀገር ገብቷልና በማለት የምህላ ጸሎት አሳወጁ። እርሳቸውም ሱባዔ ገብቶ ወደ ፈጣሪ ፀለዩ
መጋቢት 29, 1936 Gc, ግራዚያኒ እርሳቸውን ይዞ በብርብር ጎሮ (ፒያሳ) ላይ የሞት ድግስ ደገሰላቸው። ባንዳዎች ሀገርን ክዶ ከጠላት ጋር ሲያሸረግዱ አበኑ እምቢ ስላለ ለመግደል ነው የተጠሩት። የሞሶሎኒ አሸከርም ህዝብን ጠራ። ከቦ እንድያዩት አዘዘ። ወደ አቡነ ጴጥሮስ ህዶ ”ሀሳብህን ቀየርክ” አላቸው። አቡነ ጴጥሮስ አንተ የተረገምክ ፈረንጅ ያሻህን አድርግ አለው።


የመጨረሻ ሰዓት ስደርስ ስምንት ገዳዮች መስሪያ ይዞ አቡነ ጴጥሮስ ፊት ቆሙ። በጨርቅ አይኖ ይጨፈን አሉት። አቡኑም እሱ የእናንተ ስራ ነው አላቸው።
ከዛ የሞት ፅዋ ተቀበሉ። በስምንት ጥይት ተመቶ ስላልሞቶ እንደገና በሶስት ጥይት ተደብድበው አረፉ። ለሀገር ክብር፣ ለሀይማኖት ክብር ስሉ ላይመለሱ በጠላቶች ወደ ፈጣሪ ተሸኙ።
የብራ አያናን ፅሑፍ፣ ከሌሎች ወቢ ጋር በመጠቀም የቀረበ
ኦሮሞ ባንዳ ወልዶ አያቅም። ኦሮሞ እስከዛሬ ወይ ለሀገር፣ ወይም ለኦሮሙማ እየሞተ ነው የደረሰው።

By Chala Dandessa

I am Lecturer, Researcher and Freelancer. I am the founder and Editor at ETHIOPIANS TODAY website. If you have any comment use caalaadd2@gmail.com as email contact. Additionally you can contact us through the contact page of www.ethiopianstoday.com.

Leave a Reply